እንኳን ደህና መጡ ወደ ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር !!!

ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር በሐምሌ 2003 ዓ.ም ትልቅ ራዕይ በሰነቁ ሶስት ወንድማማች ኢትዮጵያውያን በንግድ ፈቃድ ቁጥር 48608/2003 የተቌቌመ ድርጅት ነው፡፡ ለድርጅቱ መቌቌም ዐብይ ምክንያት በፌደራልም ሆነ በክፍለ ሐገር የሚገኙ የስታዲየም እንዲሁም የጅምናዝየም ቁሳቁስ እና የስፖርት መሳሪያዎች አቅርቦትም ሆነ ደርጅት በአህጉር ደረጃ በተለይም በምስራቅ አፍሪካ ሲታይ አሳዛኝ ሆኖ በማግኘታቸው ነው፡፡ ይህ አሳዛኝ ሁኔታ እጅግ ስር ከመስደዱም የተነሳ በግል የተቌቌሙ ጅምናዝየም እና የጤና አጠባበቅ ማዕከላትን ጭምር ከችግሩ የፀዱ አይደሉም፡፡ ስለሆነም ድርጅቱን ያቌቌሙት ባለሀብቶች ያላቸውን ጥቂት መዋዕለ ንዋይ በማቀናጀት የስፖርት ነክ ቁሳቁሶች እና ስራዎች ያለበትን አሳዛኝ ሁኔታ ለመቀየር እና ደንበኞችን ዓለም ዐቀፍ የጥራት ደረጃ ባላቸው የስፖርት ቁሳቁሶችና መሳሪያዎች፤ በተመጣጣኝ ዋጋ፤ ውል በተገባበት ጊዜ ገደብ፤ እና ከሽያጭ በኃላ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በማቅረብ ደንበኞቻችንን በዕርካታ ለማጎናጸፍ እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ ይህንንም ዕውን ለማድረግ ድርጅቱ ላለፉት ሶስት ዓመታት ብር 8,750,000.00 (ብር ስምንት ሚሊዮን ሰባት መቶ አምሳ ሺህ) የሚገመት የመዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በስፖርት ክፍል ኢኮኖሚ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡

የአትሌቲክስ የመሮጫ ትራክ ማቅረብ እና መግጠም፤

ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር

የስፖርት ቁሳቁስ እና መሳሪያዎች በወቅቱ በማቅረብ እና በመግጠም መልካም ዝናን አትርፏል

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን እና ከኢትዮጵያ ፌደራል ሪፐብሊክ ስፖርት ኮሚሽን የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቶች አግኝቷል፡፡

የጅምናዝየም ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች ማቅረብ እና መግጠም፤

ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር

አዲስ አበባ ስታዲየም


ድርጅታችን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አዲስ አበባ ስታዲየም 450 የክቡር ትሪቢዩን መቀመጫ ወንበር እና 2,800 የተመልካቾች መቀመጫ ወንበር አቅርቦ ገጥሟል፡፡image

ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር

በድርጅቱ የተከናወኑ ስራዎች

ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር የአለም አቀፍ የጥራት ደረጃ ካሟሉ የስፖርት እና የጅምናዝየም ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች አምራች እና አቅራቢ ድንበር ተሻጋሪ ድርጅቶች ጋር መልካም የስራ ግንኙነት በመፍጠር እየሰራ ይገኛል ISO 9001-2008

image

ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር

ተጨማሪ መረጃ እና የድርጅቱ አድራሻ፤

Adidas Shoes

Negotiable Negotiable

Adidas Shoes

Negotiable Negotiable

Adidas Shoes

Negotiable Negotiable

Football Shoes

Negotiable Negotiable

asdasd

Negotiable Negotiable

hi there

Negotiable Negotiable

ሰርተፍኬት

የስታዲየም፤ የስፖርት፤ የጅምናዝየም ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች የአገር አቀፍ የጥራት መስፈርት ደረጃ ያሟሉ በመሆናቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን እና ከኢትዮጵያ ፌደራል ሪፐብሊክ ስፖርት ኮሚሽን የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቶች አግኝቷል

ካርታ