ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር

ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር በሐምሌ 2003 ዓ.ም ትልቅ ራዕይ በሰነቁ ሶስት ወንድማማች ኢትዮጵያውያን በንግድ ፈቃድ ቁጥር 48608/2003 የተቌቌመ ድርጅት ነው፡፡ ለድርጅቱ መቌቌም ዐብይ ምክንያት በፌደራልም ሆነ በክፍለ ሐገር የሚገኙ የስታዲየም እንዲሁም የጅምናዝየም ቁሳቁስ እና የስፖርት መሳሪያዎች አቅርቦትም ሆነ ደርጅት በአህጉር ደረጃ በተለይም በምስራቅ አፍሪካ ሲታይ አሳዛኝ ሆኖ በማግኘታቸው ነው፡፡ ይህ አሳዛኝ ሁኔታ እጅግ ስር ከመስደዱም የተነሳ በግል የተቌቌሙ ጅምናዝየም እና የጤና አጠባበቅ ማዕከላትን ጭምር ከችግሩ የፀዱ አይደሉም፡፡ ስለሆነም ድርጅቱን ያቌቌሙት ባለሀብቶች ያላቸውን ጥቂት መዋዕለ ንዋይ በማቀናጀት የስፖርት ነክ ቁሳቁሶች እና ስራዎች ያለበትን አሳዛኝ ሁኔታ ለመቀየር እና ደንበኞችን ዓለም ዐቀፍ የጥራት ደረጃ ባላቸው የስፖርት ቁሳቁሶችና መሳሪያዎች፤ በተመጣጣኝ ዋጋ፤ ውል በተገባበት ጊዜ ገደብ፤ እና ከሽያጭ በኃላ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በማቅረብ ደንበኞቻችንን በዕርካታ ለማጎናጸፍ እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡ ይህንንም ዕውን ለማድረግ ድርጅቱ ላለፉት ሶስት ዓመታት ብር 8,750,000.00 (ብር ስምንት ሚሊዮን ሰባት መቶ አምሳ ሺህ) የሚገመት የመዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በስፖርት ክፍል ኢኮኖሚ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡

ተልዕኮ

ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር በስፖርት ዕድገት እና በተለያዩ ዘርፎች ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ቀደምት ወይም ዋና መሪ ሆኖ ለመቀጠል ጥረት ያደርጋል።

ፍትሃዊ ዋጋ እና አገልግሎት ማቅረብ

ራዕይ

አላማችን እጅግ ጥራት ያላቸውን እቃዎች የእርስዎ ፍላጎት ባማከለ ሁኔታ እና በተስማሚ ዋጋ አገልግሎት መስጠት ነው።

የድርጅቱ መዋቅር

ደርጅቱ የተቌቌመለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በየጊዜው የሚታዩትን አካባቢያዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት የስራ መዋቅሩን እያስተካከለ ይገኛል፡፡ በመሆኑም አሁን በስራ ላይ የሚገኘው ድርጅቱ መዋቅር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ከሰባት አመት በላይ ልምድ