ጆሳምቢን ግንባቶች

ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር በተለያዩ ግንባቶች ላይ ይሰራል ።

ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር የሚከተሉትን የስታዲየም እንዲሁም የጅምናዝየም ቁሳቁስ፤ መሳሪያዎች እና የስፖርት መዝናኛ ስፍራዎች አቅርቦቶች ያደርጋል፤ በተጨማሪም ጆሳምቢን ኃ. የተ. የግል ማህበር ከስፓርት እቃ አቅርቦቶች ውጭ በሲም ካርድ አከፋፋይነት እና በኤሌክትሮኒክስ ኮምፒውተር ሽያጭ ላይ ይሰራል።


የአትሌቲክስ የመሮጫ ትራክ ማቅረብ እና መግጠም

የስታዲየም የክቡር ትሪቢዩን እና የተመልካቾች መቀመጫ ወንበሮች ማቅረብ እና መግጠም፤

የስታድየም ጣራ መግጠም እና መጠገን፤ ፤

የቮሊ ቮል መጫወቻ ሜዳ ትራክ ማቅረብ እና መግጠም፤

የስታድየም የእግር ኳስ ሜዳ ሰው ሰራሸ ሳር ማቅረብ እና መግጠም፤

የቅርጫት ኳስ መጫወቻ ሜዳ ትራክ ማቅረብ እና መግጠም

የእጅ ኳስ ሜዳ ትራክ ማቅረብ እና መግጠም፤

የስፖርት ማሰልጠኛ መሳሪያዎች ማቅረብ እና መግጠም፤

የጅምናዝየም ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች ማቅረብ እና መግጠም፤

የስፖርት ሙሉ ትጥቅ ማቅረብ እና መሸጥ፤ እና ሌሎች ስፖርት ነክ ቁሳቁሶች

በድርጅቱ የተከናወኑ ስራዎች

1. በጥቅምት 2004 ዓ.ም. ድርጅታችን ከሱር ኮንስትራክሽን ኃ. የተ. የግል ማህበር ጋር በስራ ተቌራጭነት ለፌደራል ስፖርት አካዳሚ 1,500 ስኩር ሜትር የሁለገብ መጫወቻ ሜዳ ትራክ አቅርቦ ገጥሟል፡፡ ፕሮጀክቱ ለማጠናቀቅ ብር 7,312,500.00 (ብር ሰባት ሚሊዮን ሶስት መቶ አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ፈጅቷል፡፡

2. በጥቅምት 2004 ዓ.ም. ድርጅታችን ከሱር ኮንስትራክሽን ኃ. የተ. የግል ማህበር ጋር በስራ ተቌራጭነት ለፌደራል ስፖርት አካዳሚ 1,480 መደበኛ የስታድየም መቀመጫ ወንበር፤ 150 ብረት የተገጠመለት የፕላስቲክ ወንበር እና 8 የክቡር ትሪቢዩን መቀመጫ ወንበር አቅርቦ ገጥሟል፡፡ ፕሮጀክቱ ለማጠናቀቅ ብር 3,556,960.00 (ብር ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ አምሳ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ብር) ፈጅቷል፡፡

3. በየካቲት 2004 ዓ.ም. ድርጅታችን ለአሰላ አበበ ቢቂላ ስታዲየም 818 የተመልካቾች መቀመጫ ወንበር እና 10 የክቡር ትሪቢዩን መቀመጫ ወንበር አቅርቦ ገጥሟል፡፡ ፕሮጀክቱ ለማጠናቀቅ ብር 1,015,701.30 (ብር አንድ ሚሊዮን አስራ አምስት ሺህ ሰባት መቶ አንድ ብር ከስላሳ ሣንቲም) ፈጅቷል፡፡

4. በየካቲት 2004 ዓ.ም. ድርጅታችን ለፌደራል ስፖርት ኮሚሽን ለወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የጅምናዝየም ቁሳቁሶች እና መሳሪያዎች አቅርቦ ገጥሟል፡፡ ፕሮጀክቱ ለማጠናቀቅ ብር 19,482,715.65 (ብር አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሰማንያ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ አስራ አምስት ብር ከስድሳ አምስት ሣንቲም) ፈጅቷል፡፡

5. በግንቦት 2002 ዓ.ም. ድርጅታችን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አዲስ አበባ ስታዲየም 450 የክቡር ትሪቢዩን መቀመጫ ወንበር እና 2,800 የተመልካቾች መቀመጫ ወንበር አቅርቦ ገጥሟል፡፡ ፕሮጀክቱ ለማጠናቀቅ ብር 2,373,700.00 (ብር ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰባ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ብር) ፈጅቷል፡፡


ከሰባት አመት ልምድ በላይ